13:17001:17402
Aller à la navigation
Aller à la recherche
ዛቲ፡ መልእከት፡ ዘተፈነወት፡ እምኀበ፡ አንጦንዮስ፡
ትብጸኅ፡ ኀበ፡ በአል፡ ገዳ፡ አርአያ፡ እኔስ፡ እርሶን፡ ጠልቼ፡
ሁኜ፡ በፊት፡ እኔና፡ ወንድሜ፡ ነነ፡ ወዳጆችዎ፡ ሚካኤል፡
ከርስዎ፡ እነሣለሁ፡ ሲል፡ እርሱ፡ እንዳይቀድመኝ፡ ብሎ፡
ተነሥቶ፡ መጣ፡ ቢመጣስ፡ አስቀድሞስ፡ ካድዋ፡ አልነበረም፡
ከኔ፡ አላክህ፡ ብሎ፡ ያሉኝ፡ እርሱ፡ ጠይቄ፡ አደላድዬ፡
እላካለሁ፡ ብዬ፡ ነው፡ አሁንም፡ አባ፡ ቈራንጮ፡
የራሳቸው፡ ነው፡ የላኩ፡ አባ፡ ቈራንጮ፡ ያህል፡
ደግ፡ መነኵሴ፡ ቢነግረኝ፡ ምንው፡ አላምን፡ አልወሰድሁም፡
ያለ፡ እንደሆን፡ እኔም፡ እርሱም፡ ሰው፡ እንስደድ፡
ምጥዋ፡ እንመሳከር፡ ደሞ፡ አሰት፡ እንዳይሆን፡
የርሰዎ፡ አንድ፡ ሰው፡ የሚሰማ፡ ይስደዱ፡ ውነቱ፡
አሰቱ፡ ሊገለጽ፡ እኔ፡ እንደ፡ አገራችን፡ መሰሎኝ፡
ለቴዎፍሎስ፡ ጠይቄ፡ ለምን፡ ጠየቅኸው፡ ያሉኝ፡
እንደሆን፡ ይማሩኝ፡ - እጅጉን፡ እጀጉን፡
ደኅና፡ ነዎን፡ የሰማዩን፡ የምድሩን፡ ያህል።